ለኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ዕልል ፡ በሉ (Leyesus Sem Elel Belu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ዕልል ፡ በሉ
መላዕክት ፡ ስገዱ
የመንግሥትን ፡ አክሊል ፡ አምጡ
ኢየሱስ ፡ ይቀዳጀው (፪x)

እናንት ፡ የእሥራዔል ፡ ወገን
ብትደክሙም ፡ ብታንሱም
ላዳናችሁ ፡ ዕልል ፡ በሉ
አክሊልም ፡ አምጡለት (፪x)

ወገን ፡ ነገድም ፡ ሁላችሁ
በዓለም ፡ ያላችሁ
ለኢየሱስ ፡ ስም ፡ ክብር ፡ ስጡ
አክሊልም ፡ አምጡለት (፪x)

ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ በአንድ ፡ ላይ
በግርጌው ፡ ተቀምጠን
ለዘለዓለም ፡ እንድንዘምር
ኢየሱስ ፡ ይንገሥልን (፪x)