ለኢየሱስ ፡ ልንገር (Leyesus Lenger)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ችግሬን ፡ ሁሉ
ብቻዬን ፡ ልሸከም ፡ አልችልም
ልቤ ፡ ሲጨነቅ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው
የእርሱ ፡ ከሆኑት ፡ አይለይም

አዝ፦ ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
ብቻዬን ፡ ልሸከም ፡ አልችልም
ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ረዳቴ

ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ጨንቀቴን ፡ ሁሉ
ሩህሩህ ፡ ለሆነው ፡ መልካም ፡ ወዳጅ
በጠራሁ ፡ ጊዜ ፡ ያዳምጠኛል
ችግሬንም ፡ ያጠፋልኛል

አዝ፦ ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
ብቻዬን ፡ ልሸከም ፡ አልችልም
ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ረዳቴ

በፈተና ፡ ውስጥ ፡ አዳኝ ፡ ያሻኛል
ሸክሜን ፡ ሊያግዘኝ ፡ የሚፈቅድ
ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
ሃዘኔን ፡ ለሚካፈለኝ

አዝ፦ ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
ብቻዬን ፡ ልሸከም ፡ አልችልም
ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ረዳቴ

ዓለም ፡ ለክፉ ፡ ያባብለእኛል
ልቤን ፡ ለኃጢአት ፡ ይፈትናል
ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ያስወግደዋል
ዓለምንም ፡ አሸንፋለሁ

አዝ፦ ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
ብቻዬን ፡ ልሸከም ፡ አልችልም
ለኢየሱስ ፡ ልንገር ፡ ለኢየሱስ ፡ ልንገር
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ረዳቴ