ለኢየሱስ ፡ አስረክባለሁ (Leyesus Asrekebalehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለኢየሱስ ፡ አስረክባለሁ
በነጻ ፡ እሰጣለሁ
ሁልጊዜ ፡ እወደዋለሁ
በፊቱ ፡ እኖራለሁ

አዝ፦ አስረክባለሁ ፡ አስረክባለሁ
ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ መድኃኒቴ ፡ ሆይ
አስረክባለሁ

ለኢየሱስ ፡ አስረክባለሁ
በፊቱ ፡ እሰግዳለሁ
የዓለምን ፡ ሃብት ፡ እረሳለሁ
ውሰደኝ ፡ ኢየሱስ ፡ መጣሁ

አዝ፦ አስረክባለሁ ፡ አስረክባለሁ
ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ መድኃኒቴ ፡ ሆይ
አስረክባለሁ

ለኢየሱስ ፡ አስረክባለሁ
አዳኜ ፡ የአንተ ፡ አድርገኝ
መንፈስ ፡ ቅዱስህ ፡ ይንገረኝ
የእኔ ፡ እንደሆንክልኝ

አዝ፦ አስረክባለሁ ፡ አስረክባለሁ
ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ መድኃኒቴ ፡ ሆይ
አስረክባለሁ

ለኢየሱስ ፡ አስረክባለሁ
መንፈስህን ፡ እሰማለሁ
በመድህን ፡ እደሰታለሁ
ክብር ፡ ክብር ፡ ለስሙ

አዝ፦ አስረክባለሁ ፡ አስረክባለሁ
ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ መድኃኒቴ ፡ ሆይ
አስረክባለሁ