ለውጠኝ ፡ ለውጠኝ (Lewetegn Lewetegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝለውጠኝ (፬x) ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ እንድትመስል ፡ አድርጋት
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን

እስከ ፡ መቼ ፡ ልኑር ፡ ጌታ ፡ በዚህ ፡ ሕይወት?
አንተን ፡ በማሳዘን ፡ ቁስልህን ፡ በመውጋት
መኖር ፡ አልፈልግም ፡ እያሳዘንኩ ፡ አንተን
መለወጥ ፡ እሻለሁ ፡ ፍፁም ፡ መቀየርን

አዝለውጠኝ (፬x) ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ እንድትመስል ፡ አድርጋት
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን

ሕይወቴ ፡ ይታደስ ፡ ይለወጥ ፡ ይቀየር
እኔነቴን ፡ ትቶ ፡ ክብርህን ፡ ይመስክር
በተሰበረ ልብ እንደሚልው ቃልህ
ትሁት ልሁን ጌታ ፡ ልንበርከክልህ

አዝለውጠኝ (፬x) ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ እንድትመስል ፡ አድርጋት
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን

መንፈስህ ፡ ይማርከው ፡ ሕይወቴን ፡ ይረከብ
የዓለምን ፡ ምኞት ፡ ፍፁም ፡ እንዳያስብ
ሁልጊዜ ፡ ወዳንተ ፡ ጥማት ፡ እንዲኖረኝ
ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ ሆይ ፡ ለውጠኝ ፡ ለውጠኝ

አዝለውጠኝ (፬x) ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ እንድትመስል ፡ አድርጋት
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን

ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ተጓዝኩ ፡ ርቄ ካንተ መስቀል
ኃይልን በምትሰጠኝ ባንተ ሳልታመን
ዛሬ ፡ ፈልጋለሁ እንድትለዉጠኝ
ከክብር ወደ ክብር እያሸጋገርከኝ

አዝለውጠኝ (፬x) ፡ ጌታዬ
አንተን ፡ እንድትመስል ፡ አድርጋት
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሕይወቴን