ልዑላዊ ፡ ግሩም ፡ ክብሩ (Leulawi Gerum Kebru)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ልዑላዊ ፡ ግሩም ፡ ክብሩ ፡ በእርሱ ፡ ተገለጠ
የብርሃን ፡ አክሊልን ፡ ለብሷል
ከአፉም ፡ ፀጋ ፡ ሞልቷል (፪x)
ሟች ፡ ከሆኑ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ አይወዳደርም
ከመልካሞችም ፡ መልካም ፡ ነው
ሰማይን ፡ ያደምቃል (፪x)
በችግር ፡ ውስጥ ፡ ሳለሁ ፡ አየኝ
ከጭንቄም ፡ አዳነኝ
መስቀሌን ፡ ተሸከመልኝ
ከሀዘን ፡ አዳነኝ (፪x)
በሰማይ ፡ በቅዱስ ፡ ቤቱ ፡ ከድካም ፡ አርፋለሁ
የአምላኬንም ፡ ክብር ፡ አያለሁ
ደስታዬም ፡ ፍፁም ፡ ነው ፡ (፪x)
የመለኮታዊ ፡ ፍቅሩን ፡ መግለጫ ፡ከሰጠኝ
እኔም ፡ ደግሞ ፡ በፈቃዴ
አምላክ ፡ ሆይ ፡ የአንተ ፡ ነኝ (፪x)
|