ልዑል ፡ አምላክ (Leul Amlak)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ልዑል ፡ አምላክ ፡ ለወገኑ ፡ ብዙ ፡ ስጦታ ፡ ሰጠ
ፍቅሩንም ፡ የሚያወሩ ፡ መላዕክትን ፡ ለእኛ ፡ ላከ
ልዑል ፡ አምላክ ፡ እናመስግን ፡ መላዕክትን ፡ ለላከልን

በእግዚአብሔር ፡ ልጆች ፡ ዙሪያ ፡ ፡ ይሰፍራሉ
ሊያስጥሉ ፡ ከጠላቶች ፡ ቤታቸውን ፡ ይከባሉ
በአምላክ ፡ ትዕዛዝ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት
ሊጠብቁን ፡ በጐች ፡ መላዕክት ፡ ለአምላክ ፡ ብንከተት

መንገድ ፡ ይጠርጉልናልና ፡ እግር ፡ እንዳይሰናከል
ጋሬጣን ፡ ያስነሱልናል ፡ በቃሉ ፡ እንድንከተል
ዕድሜ ፡ ቢያለማግገን ፡ ይሸከሙናል
ደስ ፡ ብሎን ፡ አምላክን ፡ እናመስግን