ለትልቅ ፡ ሥራህ ፡ ሰነፍ ፡ ነኝ (Leteleq Serah Senef Negn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለትልቅ ፡ ሥራህ ፡ ሰነፍ ፡ ነኝ
ኃይልን ፡ ፀጋን ፡ ላክልኝ
ድካሜ ፡ ኃይልህን ፡ ይግለጥ
ሥራዬ ፡ የአንተን ፡ ክብረት

ፍጠር ፡ በልቤ ፡ ቅን ፡ እምነት
ትህትናን ፡ አስርፅበት
ላከኝ ፡ መስቀልህን ፡ ልከተል
ከጭንቅ ፡ ከሞት ፡ መካከል

እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ለአንተ ፡ ነኝ
የለም ፡ የሚታጣብኝ
ከአሁን ፡ ምራኝ ፡ በአንተ ፡ ስምረት
ቁምልኝ ፡ ዕለት ፡ ዕለት