ልረፍ ፡ በኢየሱስ ፡ ክንዶች (Leref Beyesus Kendoch)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ልረፍ ፡ በኢየሱስ ፡ ክንዶች
ልረፍ ፡ በብብቱ
በፍቅሩ ፡ ከከለለኝ
ነፍሴ ፡ አትፈራም ፡ ከቶ
ስማ ፡ ከሰማይ ፡ መዝሙር
በመላዕክት ፡ ሲዘመር
በክብር ፡ የሚዘመር
በብርጭቆ ፡ ባሕር

አዝ፤
ልረፍ ፡ በኢየሱስ ፡ ክንዶች
ልረፍ ፡ በብብቱ
በፍቅሩ ፡ ከከለለኝ
ነፍሴ ፡ አትፈራም ፡ ከቶ

ልረፍ ፡ በኢየሱስ ፡ ክንዶች
ልረፍ ፡ ከሰቀቀን ፡ ልረፍ
ከዓለም ፡ ፈተና ፡ ከኃጥያትም ፡ ጭምር
ከሃዘን ፡ ነፃ ፡ ልንሆን
ደግሞም ፡ ከጥርጣሬ
ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ብቻ ፡ እንሰቃያለን

አዝ ፤
ልረፍ ፡ በኢየሱስ ፡ ክንዶች
ልረፍ ፡ በብብቱ
በፍቅሩ ፡ ከከለለኝ
ነፍሴ ፡ አትፈራም ፡ ከቶ

ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ አምባ
ስለ ፡ እኔ ፡ ሞተሃል
ዕምነቴ ፡ በዚህ ፡ አምባ
ለዘለዓለም ፡ ጸንቷል
ስለዚህም ፡ ልታገስ
ጨለማ ፡ እስኪጨረስ
የምታምረውም ፡ ንጋት
እስክትመጣ ፡ ድረስ

አዝ ፤
ልረፍ ፡ በኢየሱስ ፡ ክንዶች
ልረፍ ፡ በብብቱ
በፍቅሩ ፡ ከከለለኝ
ነፍሴ ፡ አትፈራም ፡ ከቶ