ለእኔስ ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ ቤትህ ፡ ይሻለኛል (Lenies Menem Bihon Bieteh Yeshalegnal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዛሬ ፡ የከበበኝ ፡ በዙሪያዬ
እረፍት ፡ አልሰጥ ፡ ያለው ፡ ለአእምሮዬ
የተወሳሰበው ፡ ተበጣጥሶ
እዘምራለሁ ፡ ምርኮዬ ፡ ተመልሶ
ዛሬ ፡ መስቀል ፡ ሆኖ ፡ የከበደኝ
የማመስገን ፡ መብቴን ፡ የነፈገኝ
ሲናድ ፡ ሲፈራርስ ፡ መሠረቱ
አየዋለሁ ፡ በዐይኔ ፡ በብረቱ

አዝ፦ ለእኔስ ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ ቤትህ ፡ ይሻለኛል
ባለቅስም ፡ እንባዬ ፡ ምግብ ፡ ይሆነኛል
ተመችቶኝ ፡ ይሁን ፡ ወይም ፡ ተቸግሬ
ጌታ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ይሁን ፡ መቃብሬ (፪x)

ይሆናል ፡ ያልኩት ፡ አለመሆኑ
እምነቴ ፡ ቀን ፡ በቀን ፡ መፈተኑ
አስመርሮኝ ፡ ከቤትህ ፡ ብወጣ
ምን ፡ ቸገረህ ፡ አንተ ፡ ሰው ፡ አላጣህ
ጉዳቱ ፡ ለእኔው ፡ ነው ፡ ዞሮ ፡ ዞሮ
በዓለም ፡ እጅ ፡ መጣል ፡ ተወርውሮ
መውጣት ፡ በማይቻል ፡ ስምጥ ፡ ሸለቆ
ጠውልጐ ፡ መቅረት ፡ ነው ፡ እዚያው ፡ ደርቆ

አዝ፦ ለእኔስ ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ ቤትህ ፡ ይሻለኛል
ባለቅስም ፡ እንባዬ ፡ ምግብ ፡ ይሆነኛል
ተመችቶኝ ፡ ይሁን ፡ ወይም ፡ ተቸግሬ
ጌታ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ይሁን ፡ መቃብሬ (፪x)

አንተ ፡ ዝም ፡ ብትል ፡ ለአላማህ
ጥያቄዬን ፡ ሰምተህ ፡ እንዳልሰማህ
አንድ ፡ ቀን ፡ እንባዬን ፡ ታስባለህ
በደስታ ፡ ልቤን ፡ ታስረሳለህ
የጠላቴን ፡ እራስ ፡ ትመታለህ
የረቱኝን ፡ ሁሉ ፡ ትረታለህ
የተበላሸውን ፡ ታበጃለህ
ለባርያህም ፡ ድልን ፡ ታውጃለህ

አዝ፦ ለእኔስ ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ ቤትህ ፡ ይሻለኛል
ባለቅስም ፡ እንባዬ ፡ ምግብ ፡ ይሆነኛል
ተመችቶኝ ፡ ይሁን ፡ ወይም ፡ ተቸግሬ
ጌታ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ይሁን ፡ መቃብሬ (፪x)