ለእኔስ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል (Lenies Gieta Becha Gieta Yeshalegnal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ለእኔስ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል
ሀዘኔን ፡ ችግሬን ፡ ይካፈልልኛል
በድካምም ፡ ኃይልን ፡ ድልን ፡ ይሰጠኛል

የሎጥ ፡ ዘመን ፡ ነበር ፡ ኃጢአት ፡ የበዛበት
ሰው ፡ ዓለምን ፡ ወዶ ፡ ጌታን ፡ የከዳበት
ጌታም ፡ በጣም ፡ አዝኖ ፡ እጅግም ፡ ተናዶ
ሰዶምን ፡ አጠፋ ፡ እሣትን ፡ አውርዶ

አዝ፦ ለእኔስ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል
ሀዘኔን ፡ ችግሬን ፡ ይካፈልልኛል
በድካምም ፡ ኃይልን ፡ ድልን ፡ ይሰጠኛል

በቃሉ ፡ ብሎኛል ፡ አገሬ ፡ በሰማይ ፡ ነው
እንዴት ፡ ለዓለም ፡ ነገር ፡ ጌታን ፡ ልለውጠው?
ዘመኑም ፡ ቢከፋ ፡ ብዙም ፡ ችግር ፡ ቢኖር
በጣም ፡ ይማርካል ፡ ጌታ ፡ በአንተ ፡ መኖር

አዝ፦ ለእኔስ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል
ሀዘኔን ፡ ችግሬን ፡ ይካፈልልኛል
በድካምም ፡ ኃይልን ፡ ድልን ፡ ይሰጠኛል

የሚያጽናና ፡ ወዳጅ ፡ በጐኔ ፡ ነው ፡ ጌታ
ቀጥ ፡ ብዬ ፡ ልቁም ፡ ለዓለም ፡ ሳልረታ
በክብሩ ፡ ሲገለጥ ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ከሰማይ
አብሬ ፡ እሄዳለሁ ፡ ጌታን ፡ ፊቱን ፡ እንዳይ

አዝ፦ ለእኔስ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ይሻለኛል
ሀዘኔን ፡ ችግሬን ፡ ይካፈልልኛል
በድካምም ፡ ኃይልን ፡ ድልን ፡ ይሰጠኛል