ለእኔ ፡ ምታስበው (Lenie Metasebew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የነገን ፡ እኔ ፡ አላውቅም
አንተ ፡ ግን ፡ ታውቀዋለህ
ስለዚህ ፡ እጄን ፡ ይዘህ
ምራኝ ፡ ከፊቴ ፡ ቀድመህ

አዝ፦ ለእኔ ፡ ምታስበው
በጐና ፡ መልካም ፡ ነው
ፍጻሜና ፡ ተስፋ ፡ አለው
የሰላም ፡ ሐሳብ ፡ ነው ፡ አመሰግንሃለሁ

ትምህርትህ ፡ ይጠቅመኛል
ብርሃን ፡ ለመንገዴ ፡ ሆኗል
መንፈስህ ፡ ያጽናናኛል
መንገዴን ፡ ይመራኛል

አዝ፦ ለእኔ ፡ ምታስበው
በጐና ፡ መልካም ፡ ነው
ፍጻሜና ፡ ተስፋ ፡ አለው
የሰላም ፡ ሐሳብ ፡ ነው ፡ አመሰግንሃለሁ

ደካማ ፡ ነኝ ፡ አውቃለሁ
እራሴን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ
እንደፈቃድህ ፡ ምራኝ
እንደሐሳብህ ፡ አኑረኝ

አዝ፦ ለእኔ ፡ ምታስበው
በጐና ፡ መልካም ፡ ነው
ፍጻሜና ፡ ተስፋ ፡ አለው
የሰላም ፡ ሐሳብ ፡ ነው ፡ አመሰግንሃለሁ

በጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ባልፍም
ችግር ፡ ቢደራረብም
ሁሉም ፡ ግን ፡ ለመልካም ፡ ነው
ለጥቅሜ ፡ የምታደርገው

አዝ፦ ለእኔ ፡ ምታስበው
በጐና ፡ መልካም ፡ ነው
ፍጻሜና ፡ ተስፋ ፡ አለው
የሰላም ፡ ሐሳብ ፡ ነው ፡ አመሰግንሃለሁ