ልናርፍ ፡ ነው (Lenarf New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ልናርፍ ፡ ነው ፣ ወንድም
ልናርፍ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ሊወስደን ፡ ነው (፪X)

መለከት ፡ ሊነፋ ፡ መላዕክቱን ፡ ሊያዝዝ ፡ ነው
የልጆቹን ፡ ነገር ፡ አላስችል ፡ እያለው
ጌታችን ፡ ይመጣል ፡ ከጽዮን ፡ ተራራ
ልንሄድ ፡ ነው ፡ እኛም ፡ ልንኖር ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ

አዝ፦ ልናርፍ ፡ ነው ፣ ወንድም
ልናርፍ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ሊወስደን ፡ ነው (፪X)

መሯሯጥ ፡ መባከን ፡ ይኸ ፡ ሁሉ ፡ ያበቃል
የሚያስፈልገንን ፡ ኢየሱስ ፡ አዘጋጅቷል
ዓይናችን ፡ ተከፍቶ ፡ ጌታን ፡ ልናይ ፡ ነው
እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ እኛን ፡ ሊቀበለን ፡ ነው

አዝ፦ ልናርፍ ፡ ነው ፣ እህት
ልናርፍ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ሊወስደን ፡ ነው (፪X)

እንበርታ ፡ እንጽና ፡ እንባችንን ፡ እንዋጠው
ተስፋችን ፡ ሊመጣ ፡ ሊያሳርፈን ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ነው ፡ ከመላዕክቱ ፡ ጋራ
ልናርፍ ፡ ነው ፡ እኛም ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ መከራ

አዝ፦ ልናርፍ ፡ ነው ፣ ወንድም
ልናርፍ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ሊወስደን ፡ ነው (፪X)

አዝ፦ ልናርፍ ፡ ነው ፣ እህት
ልናርፍ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ሊመጣ ፡ ሊወስደን ፡ ነው (፪X)