ልመናዬን ፡ ስለሰማኝ (Lemenayen Selesemagn)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ልመናዬን ፡ ስለ ፡ ሰማልኝ
አምላክን ፡ ልወድስ ፡ ነኝ
ረጆች ፡ ሁሉ ፡ ሲርቁብኝ
አምላክ ፡ ኃይል ፡ ረድኤት ፡ ሆነኝ
ክፉን ፡ ሁሉ ፡ ሊያሸንፍ
ሕዝቡን ፡ በሰልፉ ፡ ሊደግፍ

በጤና ፡ ወይ ፡ በሞት ፡ ጊዜ
አለኝ ፡ ተስፋ ፡ በአምላኬ
እርሱ ፡ ረድቶኛል ፡ በጭንቄ
አሁን ፡ ደስ ፡ ይላል ፡ ልቤ
ስለዚህ ፡ እርሱን ፡ ላመስግን
ለማገልገሉ ፡ ልፈጥን

ልዑል ፡ አምላክ ፡ ሁን ፡ ኃይላችን
ሕዝቡን ፡ ከሞት ፡ አድን
ማህበርህን ፡ በዓለም ፡ አግነን
ጠብቅ ፡ ግዛ ፡ ርስትህን
ተከባክበን ፡ በምድር
አልቀን ፡ በሰማይ ፡ ክብር