ልጆቹን ፡ ለማከማቸት (Lejochun Lemakemachet)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ልጆቹን ፡ ለማከማቸት
ጌታችን ፡ ሲመለስ
ጥሩ ፡ ስንዴውን ፡ ለመክተት
በክብሩ ፡ ሰገለፅ
አዝ፦ ያን ፡ ጊዜ ፡ የአምላክ ፡ ልጆች
በክብሩ ፡ ይደምቃሉ
ይበራሉም ፡ እንደ ፡ ዕንቆች
በግሩም ፡ አክሊሉ
ኢየሱስም ፡ የዋጀውን ፡ ገንዘብ
በደሙም ፡ የነጣ
ቅዱስ ፡ መንጋውን ፡ ለመሰብሰብ
ወደ ፡ እኛ ፡ ሲመጣ
አዝ፦ ያን ፡ ጊዜ ፡ የአምላክ ፡ ልጆች
በክብሩ ፡ ይደምቃሉ
ይበራሉም ፡ እንደ ፡ ዕንቆች
በግሩም ፡ አክሊሉ
ኢየሱስንም ፡ የሚወዱ
ታናናሾች ፡ ልጆች
ይሆናሉ ፡ ጌጽ ፡ በዘውዱ
የኢየሱስ ፡ ወዳጆች
አዝ፦ ያን ፡ ጊዜ ፡ የአምላክ ፡ ልጆች
በክብሩ ፡ ይደምቃሉ
ይበራሉም ፡ እንደ ፡ ዕንቆች
በግሩም ፡ አክሊሉ
|