ለእግዚአብሔር ፡ የሚሣን ፡ አለ ፡ ወይ (Legziabhier Yemisan Ale Wey)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ቀድሞ ፡ ያልነበረን ፡ ማኖር ፡ ነው ፡ ወይ
ነዋሪ ፡ የሚመስለንን ፡ ማጥፋት ፡ ነው ፡ ወይ
ከፍጡር ፡ አዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
ከእርሱ ፡ የሚወዳደር ፡ የቱ ፡ ነው

አዝለእግዚአብሔር ፡ የሚሣን ፡ አለ ፡ ወይ (፪x)
ቀድሞም ፡ አልነበረም
ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ የለም
አይኖርም ፡ ዘለዓለም

ተራራውን ፡ ሜዳ ፡ ማድረግ ፡ ነው ፡ ወይ
ባሕር ፡ ውቅያኖስን ፡ ማድረቅ ፡ ነው ፡ ወይ
ኧረ ፡ እስቲ ፡ የቱ ፡ ነው ፡ የማይችለው
በእውነት ፡ አምላካችን ፡ ታላቅ ፡ ነው

አዝለእግዚአብሔር ፡ የሚሣን ፡ አለ ፡ ወይ (፪x)
ቀድሞም ፡ አልነበረም
ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ የለም
አይኖርም ፡ ዘለዓለም

እንኳንስ ፡ በዓለም ፡ የትም ፡ የሌለ
መድህን ፡ ለበሽተኞች ፡ ሥሙ ፡ አለ
ይህ ፡ ተአምረኛ ፡ ስም ፡ ሲጠራ
ሰይጣናት ፡ ሲበኑ ፡ እንደ ፡ አቧራ

አዝለእግዚአብሔር ፡ የሚሣን ፡ አለ ፡ ወይ (፪x)
ቀድሞም ፡ አልነበረም
ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ የለም
አይኖርም ፡ ዘለዓለም

ጠላታችን ፡ ሰይጣን ፡ ሊያጠፋን
የዘለዓለምን ፡ ሞት ፡ ሊያወርሰን
ግን ፡ ቸሩ ፡ አምላካችን ፡ ራራልን
ሞታችንን ፡ ሞቶ ፡ አዳነን

አዝለእግዚአብሔር ፡ የሚሣን ፡ አለ ፡ ወይ (፪x)
ቀድሞም ፡ አልነበረም
ዛሬም ፡ ቢሆን ፡ የለም
አይኖርም ፡ ዘለዓለም