ለእኛ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው (Legna Yegelet Zend Kalew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ለእኛ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ጋር ፡ ቢመዛዘን
የአሁኑ ፡ ዘመን ፡ ስቃይ ፡ ምንም ፡ እንዳይደለ ፡ እናስባለን
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እያለፍን ፡ እንገሠግሳለን
ተስፋችን ፡ በጌታ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ድል ፡ እንነሳለን

ረዳት ፡ የሌላቸው ፡ ምስኪኖች ፡ እንመስላለን
መዘበቻ ፡ ሆነን ፡ ተንቀን ፡ እንኖራለን
ጠንክረን ፡ ብንቆይ ፡ መከራችንን ፡ ታግሰን
ዘመኑ ፡ ሲፈጸም ፡ ከውርደት ፡ ተነስተን
ከጌታ ፡ ጋር ፡ እንከብራለን

አዝ፦ ለእኛ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ጋር ፡ ቢመዛዘን
የአሁኑ ፡ ዘመን ፡ ስቃይ ፡ ምንም ፡ እንዳይደለ ፡ እናስባለን
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እያለፍን ፡ እንገሠግሳለን
ተስፋችን ፡ በጌታ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ድል ፡ እንነሳለን

ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ነው ፡ የእምነታችን ፡ መፈተን
ከብድራቱ ፡ ጋር ፡ መከራችን ፡ ሲመዛዘን
አይቆጨንም ፡ ከቶ ፡ የማይጠፋ ፡ ክብር ፡ አለን
ቁም ፡ ነገር ፡ ነውና ፡ ረባችንን ፡ ጥለን
ለዚህ ፡ እንጋደላለን

አዝ፦ ለእኛ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ጋር ፡ ቢመዛዘን
የአሁኑ ፡ ዘመን ፡ ስቃይ ፡ ምንም ፡ እንዳይደለ ፡ እናስባለን
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እያለፍን ፡ እንገሠግሳለን
ተስፋችን ፡ በጌታ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ድል ፡ እንነሳለን

በትዕግሥት ፡ የጸኑ ፡ በእርግጥ ፡ ብጹዐን ፡ ናቸው
በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጸንተው ፡ ባልመድከማቸው
ያለፉትን ፡ እንይ ፡ ምስክሮቻችን ፡ ናቸው
ከድካም ፡ ያረፉ ፡ ቅዱሳን
እነሆ ፡ ጌታ ፡ ያላፈረባቸው

አዝ፦ ለእኛ ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ጋር ፡ ቢመዛዘን
የአሁኑ ፡ ዘመን ፡ ስቃይ ፡ ምንም ፡ እንዳይደለ ፡ እናስባለን
ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እያለፍን ፡ እንገሠግሳለን
ተስፋችን ፡ በጌታ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ድል ፡ እንነሳለን