ለደስታ ፡ ቀን (Ledesta Qen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለደስታ ፡ ቀን ፡ ሆነ ፡ ንጋት
ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ሆነላት
መሲህ ፡ እንደ ፡ ተወለደ
ለእረኞች ፡ ተገለጠ

በደንባሮች ፡ በጐች ፡ መሃል
በጐ ፡ እረኛ ፡ ገብቷል
የከዱትንም ፡ ይጠራል
ሰባሮችን ፡ ይጠግናል

ትሁት ፡ ሩኅሩኅ ፡ ሆኖ ፡ መጣ
እስከ ፡ ሞት ፡ መስቀል ፡ ሊገዛ
ከሞት ፡ በደሙ ፡ ሊዋጀን
ዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ሊሰጠን

ለጋ ፡ ተክል ፡ የመሰለች
ታላቅ ፡ ዛፍ ፡ ሁና ፡ ጀበበች
የማህበር ፡ ጫፎች ፡ በዓለሙ
ለደከሙ ፡ ያጠጣሉ

ዝናብ ፡ ምድርን ፡ እንዳራሳት
ቃሉ ፡ ሊሰጥ ፡ ደስታ ፡ ልማት
ፅድቅን ፡ ሰላምን ፡ ያመጣል
ፍሬ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያፈራል

ሰማይና ፡ ምድር ፡ ያልፋል
የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ ግን ፡ ይኖራል
ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ሊሰግዱ
ቋንቆች ፡ ሥሙን ፡ ሊታመኑ

በኢየሱስ ፡ ኃይል ፡ ኦ ፡ ክርስቲያን
ተነሱና ፡ ሁኑ ፡ ብርሃን
የታገለ ፡ ድል ፡ ይነሳል
የታገሰ ፡ ይከብራል

ለቸር ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ስብሓት
ስላሳየን ፡ ፍቅር ፡ የውሃት
በምህረቱ ፡ ስላዳነን
እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ይመሥገን