ለአምላክ ፡ ዘምሩ (Leamlak Zemeru)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ለአምላክ ፡ ዘምሩ!
በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይበለን!
በታላቅ ፡ ፍቅሩ
ግሩም ፡ ውለታ ፡ ሠራልን
ከእናት ፡ ማሕጸን
በምሕረት ፡ እስካሁን
ወትሮ ፡ ሲጠብቀን
ሠራልን ፡ መልካሙን

የፀጋ ፡ አምላክን
ወትሮ ፡ እንድንፈራ
መንፈሱንም ፡ ይስጠን
በእርሱም ፡ እንመራ
የምሕረት ፡ አምላክም
ይስጠነ ፡ ምሕረቱን
እስከ ፡ ዘለዓለምም
ከእኛ ፡ ጋር ፡ ይሁን

ሠርክ ፡ እናመስግንህ!
ኦ! ዓብ ፣ ኦ! ወልድ ፣ ኦ! መንፈስ!
ዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነህ!
ኦ! አንተ ፡ ሥሉስ ፡ ቅዱስ!
ለቅዱስ ፡ ሥላሴ
ለሦስቱ ፡ አካላት
እናቅርብ ፡ ውዳሴ
እናቅርብም ፡ ስብሐት!