ለአምላክ ፡ በሰማይ ፡ ቀኙ (Leamlak Besemay Qegnu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለአምላክ ፡ በሰማይ ፡ ቀኙ
ሕዝቦች ፡ ሁሉ ፡ ይስገዱ
ድምጽ ፡ ያለበት ፡ ነፍስ ፡ ሁሉ
ያመስግን ፡ በመቅደሱ

በእጁ ፡ የፈጠረው
እጅግ ፡ ግሩምና ፡ መልካም ፡ ነው
ከዘለዓለም ፡ ያሳየው
ተገልጦልን ፡ ግርማው

ከአምላክ ፡ ላስታረቀን
ከጥፋት ፡ ለነጠቀን
እንደ ፡ አባት ፡ ላሞገሰን
እንዘምር ፡ ሁሉ ፡ ቀን

ፍጥረቱ ፡ በመላዋ
ስብሐት ፡ ታቅርብ ፡ ለጌታ
ነፍሴም ፡ ደግሞ ፡ በደስታ
ታመስግን ፡ ሃሌ ፡ ሉያ