ለዓለም ፡ ሕይወት (Lealem Hiwot)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ልትዋጅ
ሥጋችንን ፡ ለብሰህ
ተስፋችንን ፡ ልታዘጋጅ
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞትን ፡ ቀመስህ
ያለ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ በጠፋነ
ሲዖል ፡ ተከፈተብነ
ሞትም ፡ ርስታችን ፡ ነበር

አንተም ፡ ስታይ ፡ የእኛን ፡ ጉዳት
በፍቅርህ ፡ ራራህልን
ልታድነንም ፡ ከጥፋት
ወደ ፡ ዓለም ፡ ወረድህልን
ከአንተ ፡ ሞትና ፡ ሕማም
የእግዚአብሔር ፡ ሰላም
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ተገኘልን

በትሩፋትህ ፡ አምነን
ወደ ፡ አምላክ ፡ ስንመጣ
ሙሉ ፡ ይቅርታ ፡ ሰጠኸን
በሕግ ፡ እንዳንቀጣ
እኛም ፡ ይህን ፡ ተቀብለን
በቅድስ ፡ ቃልህ ፡ ታምነን
ከሞት ፡ እንድናለን

ቸር ፡ ወንድማችን ፡ አንተ ፡ ነህ
እንዴት ፡ አክብረኸናል
ዘለዓለም ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ነህ
ሁሉንም ፡ ሰጥተኸናል
የዓለም ፡ ስድብና ፡ ጥል
ከቶ ፡ ሊጐዳን ፡ እንዳይችል
አምባችን ፡ የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ነው

ግሩም ፡ ፀጋህ ፡ የሰጠኸን
መድኃኒት ፡ ሆይ ፡ ተወደስ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ልጆች ፡ ነን
ኦ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
አምላክን ፡ እናመስግንም
እርሱ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሥም
ቸር ፡ አባታችን ፡ ሆነ