ለኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ይሁን ፡ ስብሐት (LeEyesus Sim Yihun Sibhat)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ለኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ይሁን ፡ ስብሐት
ኑ ፡ ለርሱ ፡ ስገዱለት
መሥዋዕትንም ፡ አቅርቡለት
ኦ! ይንገሥ ፡ ይንገሥ
ንጉሠ ፡ ስብሐት!

በደሙ ፡ የተገዛችሁ
ከሞትም ፡ የዳናችሁ
ስገዱለት ፡ ላነጻችሁ
ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ
ልዑል ፡ ጌታችሁ!

ለርሱ ፡ ይሁን ፡ ምሥጋናችን
ለልዑል ፡ አምላካችን
እናንግሠው ፡ በልባችን
ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ
መድኃኒታችን!