ላይህ ፡ እናፍቃለሁ (Layeh Enafeqalehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ብርሃን ፡ ብርሃኔ ፡ ለእኔ ፡ ሆኖ
በመንገዴ ፡ አንተን ፡ እያየሁ
ያወጅኩትን ፡ ሞትህን ፡ ቀምሼ
በትንሳኤ ፡ ልምሰልህ ፡ እርዳኝ

አዝ፦ ላይህ ፡ እናፍቃለሁ
ጌታ ፡ እናፍቅሃለሁ
ላይህ ፡ እናፍቃለሁ ፡ ጌታዬ
የእጆችህን ፡ ቁስል
የእግሮችህን ፡ ቁስል
የተወጋው ፡ የቀኝ ፡ ጐንህን

እንባዬ ፡ ይሰማህ ፡ ከዙፋንህ
ብሩህ ፡ ሗህንም ፡ ሰንጥቆ
ነፍሴ ፡ የምታርፍበት ፡ አጣች ፡ ጌታ
መቼ ፡ ነው ፡ የማይህ ፡ ስትመጣ

አዝ፦ ላይህ ፡ እናፍቃለሁ
ጌታ ፡ እናፍቅሃለሁ
ላይህ ፡ እናፍቃለሁ ፡ ጌታዬ
የእጆችህን ፡ ቁስል
የእግሮችህን ፡ ቁስል
የተወጋው ፡ የቀኝ ፡ ጐንህን

ሁሉን ፡ ለመፈጸም ፡ ጌታ ፡ ሲታይ
ክብሩን ፡ አንሠራፍቶ ፡ በሰማይ
ልጆቹን ፡ ለመንጠቅ ፡ ሲልክ ፡ እጁን
ምን ፡ ስሰራ ፡ ያገኘኝ ፡ ይሆን

አዝ፦ ላይህ ፡ እናፍቃለሁ
ጌታ ፡ እናፍቅሃለሁ
ላይህ ፡ እናፍቃለሁ ፡ ጌታዬ
የእጆችህን ፡ ቁስል
የእግሮችህን ፡ ቁስል
የተወጋው ፡ የቀኝ ፡ ጐንህን

በተጠራ ፡ ጊዜ ፡ ቃሌን ፡ ሰምቶ
ያልጠበቀኝ ፡ በጊዜው ፡ ነቅቶ
ዕድሉን ፡ ያጐድላል ፡ ብሏልና
ነፍሴ ፡ ሳትደክም ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ና

አዝ፦ ላይህ ፡ እናፍቃለሁ
ጌታ ፡ እናፍቅሃለሁ
ላይህ ፡ እናፍቃለሁ ፡ ጌታዬ
የእጆችህን ፡ ቁስል
የእግሮችህን ፡ ቁስል
የተወጋው ፡ የቀኝ ፡ ጐንህን