ለአምላካችን ፡ በሰማይ (Lamlakachen Besemay)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

<poem>
ለአምላካችን ፡ በሰማይ
ይገባዋል ፡ ምሥጋና
ስለ ፡ ፀጋው ፡ በሰው ፡ ላይ
የሰጠው ፡ ለብፅዕና
በምድር ፡ ደስታና ፡ ሰላም
ሲሰጥ ፡ ይገባናል ፡ በጣም
ፈቃድን ፡ ልንፈጽም

ኦ ፡ አባት ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ምህረት
እናመሰግናለን
አንተ ፡ በታላቅ ፡ ቸርነት
ፀጋን ፡ አወረድህልን
ስሉጥ ፡ እጅህ ፡ ሁሉን ፡ ይይዛል
ስውር ፡ ኃጢያት ፡ ይታይሃል
ዳኝነትህ ፡ ይቀናል

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የልዑል ፡ ልጅ
ልታድነን ፡ የመጣህ
ከፍርድና ፡ ከሰይጣን ፡ እጅ
በሞት ፡ እኛን ፡ የዋጀህ
በትልቅ ፡ ምህረትህ ፡ መጠን
ከመቅሰፍት ፡ ሞት ፡ ልታድነን
በአንተ ፡ ስንማጠን

በመንፈስህ ፡ ልባችንን
በቃልህ ፡ አጽናና
ለአንተ ፡ ምሥጋና ፡ መቅደስህን
ወደ ፡ ነፍሳችን ፡ ሥራ
በመከራችን ፡ ደግፈን
አድስ ፡ ለፅድቅ ፡ ልባችንን
እምነትን ፡ ጨምርልን
</poem>