ለአምላክ ፡ ዘምሩ (Lamlak Zemeru)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለአምላክ ፡ ዘምሩ ፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይበለን
በታላቅ ፡ ፍቅሩ ፡ ግሩም ፡ ውለታ ፡ ሰራልን
ከእናት ፡ ማህፀን ፡ በምህረት ፡ እስካሁን
ወትሮ ፡ ሲጠብቀን ፡ ሰራልን ፡ መልካሙን

የፀጋ ፡ አምላክን ፡ ወትሮ ፡ እንድንፈራ
መንፈሱንም ፡ ይስጠን ፡ በእርሱም ፡ እንመራ
የምህረት ፡ አምላክም ፡ ይስጠን ፡ ምህረቱን
እስከ ፡ ዘለዓለምም ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ይሁን

ሰርክ ፡ እናመስግንህ
ኦ ፡ አብ ፡ ኦ ፡ ወልድ ፡ ኦ ፡ መንፈስ
ዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነህ
ኦ ፡ አንተ ፡ ሥሉስ ፡ ቅዱስ
ለቅዱስ ፡ ሥላሴ ፡ ለሦሥቱ ፡ አካላት
እናቅርብ ፡ ውዳሴ ፡ እናቅርብም ፡ ስብሓት