ላመስግንህ ፡ ጌታ (Lamesgeneh Gieta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ለእኔ ፡ ስላረከው ፡ ብዙ ፡ ስራህ
እንዲያው ፡ ቢሆንልኝ ፡ ለውለታህ
ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ

የተረሳሁ ፡ ነበርኩ ፡ የተጣልኩኝ
ውዴ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ባትፈልገኝ
ከጉድፍ ፡ ከአመድ ፡ አንስተኸኝ
ከቅዱሳንህ ፡ ጋር ፡ አከበርከኝ (ላመስግንህ)

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ለእኔ ፡ ስላረከው ፡ ብዙ ፡ ስራህ
እንዲያው ፡ ቢሆንልኝ ፡ ለውለታህ
ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ

በዐይን ፡ የሚሞሉ ፡ ታላላቆች
እያሉ ፡ የከበሩ ፡ ብዙ ፡ ሰዎች
ነፍስ ፡ ዘርተህብኝ ፡ የሞትኩትን
አገልጋይ ፡ አደረከኝ ፡ ለአንተ ፡ የማጥን (ላመስግንህ)

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ለእኔ ፡ ስላረከው ፡ ብዙ ፡ ስራህ
እንዲያው ፡ ቢሆንልኝ ፡ ለውለታህ
ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ

ጌታ ፡ ትገድላለህ ፡ ታድናለህ
ሲኦል ፡ ታወርዳለህ ፡ ታወጣለህ
ድሃ ፡ ታደርጋለህ ፡ ባለፀጋ
ሐሳብህን ፡ የለም ፡ የሚከለክል (ላመስግንህ)

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ለእኔ ፡ ስላረከው ፡ ብዙ ፡ ስራህ
እንዲያው ፡ ቢሆንልኝ ፡ ለውለታህ
ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ

ልቤ ፡ በአንተ ፡ ጸንቷል ፡ መድሃኒቴ
አፌም ፡ ተከፈተና ፡ በጠላቴ
ደስ ፡ ብሎኛልና ፡ በማዳንህ
ሞገስ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ይስፋ ፡ ክብርህ (ላመስግንህ)

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ለእኔ ፡ ስላረከው ፡ ብዙ ፡ ስራህ
እንዲያው ፡ ቢሆንልኝ ፡ ለውለታህ
ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ

አምላኬ ፡ ሰው ፡ ሆንኩኝ ፡ በአንተ ፡ ስራ
ጠዋት ፡ ማታ ፡ ስምህን ፡ የምጠራ
ኢየሱስ ፡ በመቅደስህ ፡ በማደሪያህ
ምሥጋናዬ ፡ ይድረስ ፡ ወደፊትህ (ላመስግንህ)

አዝ፦ ላመስግንህ ፡ ጌታ ፡ ላመስግንህ
ለእኔ ፡ ስላረከው ፡ ብዙ ፡ ስራህ
እንዲያው ፡ ቢሆንልኝ ፡ ለውለታህ
ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ