From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አንደበት ፡ የለኝ ፡ ስምህን ፡ ልጠራ
ምላሥም ፡ የለኝ ፡ ሥራህን ፡ ላወራ
ልናገርም ፡ ብል ፡ ጊዜው ፡ አይበቃ
ተመስገን ፡ ብዬ ፡ በአጭሩ ፡ ላብቃ
አዝ ፣
ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ ውስጤም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና ።
በፍቅር ፡ ቃልህ ፡ ልቤን ፡ ስትመታ
ነፍሰ ፡ ሥጋዬን ፡ ከእሥር ፡ ልትፈታ
ምን ፡ አለኝና ፡ ምንን ፡ ልክፈልህ?
ከተቀበልኸኝ ፡ ክበር ፡ ልበልህ
አዝ ፣
ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ ውስጤም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና ።
ከትቢያ ፡ አንስተህ ፡ ሰው ፡ ስታደርገኝ
በነፍስ ፡ በሥጋ ፡ ስትባርከኝ
ሰማያዊ ፡ ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ሲሞላ
ተመስገን ፡ እንጂ ፡ የለኝም ፡ ሌላ
አዝ ፣
ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ ውስጤም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና ።
|