ለአዳኜ ፡ እዘምራለሁ (Ladagnie Ezemeralehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እዘምራለሁ ፡ ለአዳኜ
ላስደናቂው ፡ ፍቅሩ ፡ ሲል
ተሰቃየልኝ ፡ በመስቀል
ከመርገም ፡ እኔን ፡ ሊያድን

አዝ፦ ዘምሩ ፡ ለአዳኜ ፡ ክብር
ለአዳኜ ፡ ክብር ፡ ዘምሩ
ለአዳኜ ፡ ክብር
በደሙ ፡ እኔን ፡ ገዛኝ
እኔን ፡ ገዛኝ ፡ በደሙ
እኔን ፡ ገዛኝ

ድንቁን ፡ ታሪክ ፡ እነግራለሁ
ከጥፋቴ ፡ እንዳዳነኝ
ሰፊ ፡ በሆነው ፡ ምህረቱ
በትርፍ ፡ ሁሉን ፡ ለሰጠኝ

አዝ፦ ዘምሩ ፡ ለአዳኜ ፡ ክብር
ለአዳኜ ፡ ክብር ፡ ዘምሩ
ለአዳኜ ፡ ክብር
በደሙ ፡ እኔን ፡ ገዛኝ
እኔን ፡ ገዛኝ ፡ በደሙ
እኔን ፡ ገዛኝ

ውድ ፡ አዳኜን ፡ ላመስግነው
ድል ፡ ነሺ ፡ ኃይሉን ፡ ልንገር
በሞትና ፡ ሲዖል ፡ ላይ
አሸናፊ ፡ ላረገኝ

አዝ፦ ዘምሩ ፡ ለአዳኜ ፡ ክብር
ለአዳኜ ፡ ክብር ፡ ዘምሩ
ለአዳኜ ፡ ክብር
በደሙ ፡ እኔን ፡ ገዛኝ
እኔን ፡ ገዛኝ ፡ በደሙ
እኔን ፡ ገዛኝ

እዘምራለሁ ፡ ለአዳኜ
ለሰማያዊ ፡ ፍቅሩ
ከሞት ፡ ሕይወትን ፡ አሳየኝ
በእርሱም ፡ ያምላክ ፡ ልጅ ፡ ሆንኩኝ

አዝ፦ ዘምሩ ፡ ለአዳኜ ፡ ክብር
ለአዳኜ ፡ ክብር ፡ ዘምሩ
ለአዳኜ ፡ ክብር
በደሙ ፡ እኔን ፡ ገዛኝ
እኔን ፡ ገዛኝ ፡ በደሙ
እኔን ፡ ገዛኝ