ክርስቶስ ፡ ዛሬ ፡ ተነሥቷል (Kristos Zarie Tenestoal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ክርስቶስ ፡ ዛሬ ፡ ተነሥቷል
ሃሌ ፡ ሉያ !
ቅዱስ ፡ ቀናችን ፡ ነግቷል
ሃሌ ፡ ሉያ !
በመስቀል ፡ የሞተልን
ሃሌ ፡ ሉያ !
ዕዳችንን ፡ ሊያስወግድልን
ሃሌ ፡ ሉያ !

ለክርስቶስ ፡ ንጉሠ ፡ ስብሓት
ሃሌ ፡ ሉያ !
ውዳሴን ፡ እናቅርብለት
ሃሌ ፡ ሉያ !
በመቃብር ፡ ለተኛ
ሃሌ ፡ ሉያ !
ሕይወት ፡ ይሰጥ ፡ ዘንድ ፡ ለኃጢአተኛ
ሃሌ ፡ ሉያ !

በሥቃዩ ፡ አዳነን
ሃሌ ፡ ሉያ !
መድኃኒትም ፡ ሆነልን
ሃሌ ፡ ሉያ !
አሁን ፡ በላይ ፡ ነግሦአል
ሃሌ ፡ ሉያ !
መላዕክትም ፡ በዙሪያው ፡ ቆመዋል
ሃሌ ፡ ሉያ !

ምሥጋና ፡ ለአምላካችን
ሃሌ ፡ ሉያ !
እናቅርብ ፡ ከልባችን
ሃሌ ፡ ሉያ !
ዓለም ፡ ምሉ ፡ ይቀደስ
ሃሌ ፡ ሉያ !
ለዓብ ፡ ለወልድ ፡ ለመንፈስ ፡ ቅዱስ
ሃሌ ፡ ሉያ !