ከዘላለም ፡ የወጣ ፡ መለኮታዊ ፡ ፀሐዩ (Kezelalem Yewetta Melekotawi Tsehayu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከዘላለም ፡ የወጣ
መለኮታዊ ፡ ፀሐዩ
በዚህ ፡ ቀን ፡ ለእኛ ፡ ይብራ
ያሙቀን ፡ ድሙቅ ፡ ብርሃኑ
ለወጠልን ፡ ጨለማን
ለብርሃን

አርስ ፡ ደረቅ ፡ ሕሊናን
አውርድ ፡ መንፈሣዊ ፡ ጤዛን
አድርገም ፡ ፍሬያም ፡ እርሻን
ለሚጠቅም ፡ ሥራ ፡ አትጋን
በመንፈስ ፡ አጠንክረን
ቀስቅሰን

በሚግል ፡ በአንተ ፡ ፍቅር
ክፉን ፡ ዓመላችን ፡ መዝብር
ልንኖር ፡ ለአንተ ፡ ክብር
ዓርበኝነት ፡ በኛ ፡ ፍጠር
የአንተን ፡ መንግሥት ፡ ለማስፋት
ስጥ ፡ ቅናት

አንተ ፣ የሰማይ ፡ ብርሃን
ከዓለም ፡ ጨለማ ፡ አስወጣን
አርቅልን ፡ ስንፍናን
ወደ ፡ አምላክ ፡ ግርማ ፡ አግባን
ደስታ ፡ በሚገኝበት
በምላት

የፍርድ ፡ ቀን ፡ ሲደርስብን
ፀጋን ፡ ምሕረትን ፡ አሳየን
በክብረትህ ፡ ሸልመን
ለውጥልን ፡ ውርደታችን
አድለነ ፡ በፀጋ
ብፅዕና