ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ በደህና ፡ እሄዳለሁ (Keyesus Gar Bedehna Ehiedalehu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ በደኅና ፡ እሄዳለሁ
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ላይ ፡ በእርሱ ፡ ከተመራሁ
ያለ ፡ እርሱ ፡ ደስታዬ ፡ ከንቱ ፡ ይሆናል
እርሱ ፡ ግን ፡ ፍርሃትን ፡ ሁሉ ፡ ያጠፋል

አዝ ፤
ከማንም ፡ ከማንም ፡ ከቶ ፡ አልፈራም
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ በደኅና ፡ እሄዳለሁ

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ከእኔ ፡ ከቶ ፡ አይርቅም
ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ ሲረሳ ፡ አይረሳኝም
እጆቹ ፡ በጭንቁ ፡ መንገድ ፡ ቢመሩኝ
ከእርሱ ፡ ዘንድ ፡ የምሥጋና ፡ ቤት ፡ አለልኝ

አዝ ፤
ከማንም ፡ ከማንም ፡ ከቶ ፡ አልፈራም
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ በደኅና ፡ እሄዳለሁ

ከኢየሱሴ ፡ ጋር ፡ በሰላም ፡ አርፋለሁ
በሌሊት ፡ ጨለማ ፡ ስከበብ ፡ ሳለሁ
በደስታ ፡ እንደምነቃም ፡ አውቃለሁ
በሚያምረውም ፡ ቤት ፡ አብሬ ፡ እኖራለሁ

አዝ ፤
ከማንም ፡ ከማንም ፡ ከቶ ፡ አልፈራም
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ በደኅና ፡ እሄዳለሁ