ከሰማይ ፡ ማን ፡ ወረደ (Kesemay Maan Worede)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከሰማይ ፡ ማን ፡ ወረደ?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
በጐል ፡ ማን ፡ ተወለደ?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ዘምሩ ፡ ለክብረቱ
በእርሱ ፡ ነው ፡ ደኅንነቱ
እርሱ ፡ ነው ፡ መድኃኒቱ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።

ማን ፡ ሞተ ፡ በጐልጐታ?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ከሞት ፡ እኛን ፡ ሊፈታ
ሞተ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ዘምሩ ፡ ለክብረቱ
በእርሱ ፡ ነው ፡ ደኅንነቱ
እርሱ ፡ ነው ፡ መድኃኒቱ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።

ማን ፡ ነው ፡ ፈቃር ፡ ሁሉ ፡ ቀን?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ማን ፡ ይላል ፡ ብታምን ፡ ዳን?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ዘምሩ ፡ ለክብረቱ
በእርሱ ፡ ነው ፡ ደኅንነቱ
እርሱ ፡ ነው ፡ መድኃኒቱ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።

በሰማይ ፡ ዙፋን ፡ ማን ፡ ነው?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
በዕምነት ፡ የምናየው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ዘምሩ ፡ ለክብረቱ
በእርሱ ፡ ነው ፡ ደኅንነቱ
እርሱ ፡ ነው ፡ መድኃኒቱ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።

ማን ፡ ይመለሳል ፡ ከላይ?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ማን ፡ ያወርሰናል ፡ ሰማይ?
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።
ዘምሩ ፡ ለክብረቱ
በእርሱ ፡ ነው ፡ ደኅንነቱ
እርሱ ፡ ነው ፡ መድኃኒቱ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ።