ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ (Keselemon Yemibelt)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኀጢአት ፡ ላደቀቀው ፡ ወጥመድ ፡ ውስጥ ፡ ላገባው
በጥያቄ ፡ ማዕበል ፡ ግራ ፡ ለተጋባው
የውስጥ ፡ ስቆቃን ፡ ጠልቆ ፡ የሚያዳምጥ
ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ አለ ፡ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ (፪x)

አዝ፦ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ ፡ ተአምር ፡ የሚሰራ
እንቆቅልሽ ፡ ፈቺ ፡ አለ ፡ በዚህ ፡ ስፍራ
መሃትሙን ፡ የፈታ ፡ ኢየሱስ
የሠማይ ፡ የምድር ፡ ንጉሥ

የመቃብር ፡ ደወል ፡ የሞት ፡ ድምጽ ፡ ላወደው
መኖር ፡ ለመረረው ፡ ሕይወቱን ፡ ለጠላው
ተዐምር ፡ የሚሰራ ፡ ዳግም ፡ ልደት ፡ የሚሰጥ
ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ አለ ፡ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ (፪x)

አዝ፦ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ ፡ ተአምር ፡ የሚሰራ
እንቆቅልሽ ፡ ፈቺ ፡ አለ ፡ በዚህ ፡ ስፍራ
መሃትሙን ፡ የፈታ ፡ ኢየሱስ
የሠማይ ፡ የምድር ፡ ንጉሥ

የሰው ፡ ጉዳት ፡ የሚያውቅ ፡ የልብ ፡ አማካሪ
የክንፉ ፡ እስርአት ፡ ሰንሰለት ፡ ሰባሪ
ጨለማን ፡ የሚያበራ ፡ ምስጢርን ፡ የሚገልጥ
ኢየሱስ ፡ ከዚህ ፡ አለ ፡ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ (፪x)

አዝ፦ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ ፡ ተአምር ፡ የሚሰራ
እንቆቅልሽ ፡ ፈቺ ፡ አለ ፡ በዚህ ፡ ስፍራ
መሃትሙን ፡ የፈታ ፡ ኢየሱስ
የሠማይ ፡ የምድር ፡ ንጉሥ

ዘመድ ፡ እርቆ ፡ ሲቆም ፡ ወዳጅም ፡ ሲከዳው
በጨለማ ፡ ሲሆን ፡ ደርሶ ፡ የሚረዳው
ጭው ፡ ባለ ፡ ሌሊት ፡ ዝማሬን ፡ የሚሰጥ
ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ አለ ፡ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ (፪x)

አዝ፦ ከሰለሞን ፡ የሚበልጥ ፡ ተአምር ፡ የሚሰራ
እንቆቅልሽ ፡ ፈቺ ፡ አለ ፡ በዚህ ፡ ስፍራ
መሃትሙን ፡ የፈታ ፡ ኢየሱስ
የሠማይ ፡ የምድር ፡ ንጉሥ

የሰላም ፡ ጌታ ፡ የጠቢባን ፡ አምላክ
ከእርሱ ፡ የተሰወረ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሚደበቅ
ተስፋ ፡ ለቆረጠ ፡ ድረስለኝ ፡ ላለ
ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ በዚህ ፡ አለ (፪x)