ክርስቶስ ፡ ህይው ፡ ሆነ (Kerestos Heyaw Hone)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ክርስቶስ ፡ ሕያው ፡ ሆነ ፡ መቃብር ፡ በራ
መድሃኒቴ ፡ ተገኘ ፡ ትንቢትም ፡ ሞላ
ግርማን ፡ ተጐናጽፎ ፡ ከሞት ፡ ተነሳ
ጠላት ፡ ተሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ
ማኅተሙ ፡ ተፈታ ፡ ድንጊያው ፡ ለቀቀ
ጠባቂውም ፡ ፈርቶ ፡ ፈጥኖ ፡ ሸሸ
ሲኦልም ፡ ተፈዛ ፡ ሃሌሉያ

ከጨለማ ፡ ጋራ ፡ ብርሃን ፡ ሲዋጋ
ብርሃን ፡ ለዘለዓለም ፡ ፍፁም ፡ ድል ፡ ነሳ
ያ ፡ ሞት ፡ ተደባየ
ድል ፡ ነሳ ፡ ሕይወት
ተስፋችን ፡ በረታ ፡ ለማጽናት ፡ እምነት
እናንተ ፡ ሃዘንተኞች ፡ ከልብ ፡ ተቀኙ
ከሞት ፡ አዳነን ፡ በቸርነቱ
ሊኖር ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ሃሌሉያ

ሠማይ ፡ ከምድራችን ፡ አሁን ፡ ታርቆናል
መቃብር ፡ የደስታ ፡ መንገድ ፡ ሆኗል
በመስቀል ፡ ትይዩ ፡ ያለቀሳቹህ
ሞት ፡ ተሸንፏል ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ
ከዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ የጠፉት ፡ ሁሉ
ወደ ፡ ቸር ፡ ኧረኛ ፡ ይመለሳሉ
ሕይወት ፡ ያገኛሉ ፡ ሃሌሉያ

ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ጸናች ፡ ነፍሳትም ፡ ይምጡ
በብርሃኑ ፡ ፍጥነት ፡ ሰፋ ፡ ትምህርቱ
በዓለሙ ፡ ወጡ ፡ መልእክተኞቹ
ሞት ፡ እንኳን ፡ ሳይፈሩ ፡ ወንጌል ፡ ሲሰብኩ
ስለእኛ ፡ ለሞተ ፡ ነጻ ፡ ላወጣን
ምስክር ፡ ሲሰጡ ፡ ሰውን ፡ ለማዳን
ሊጣሩ ፡ በደስታ ፡ ሃሌሉያ

ለምን ፡ ታዝናላችሁ ፡ እናንተ ፡ መዕመናን?
አጭር ፡ ነው ፡ ዘመኑ ፡ ሞት ፡ እስኪጠራን
መሬት ፡ እንደ ፡ እናት ፡ ልታቅፋችሁ
እንደ ፡ ሕያው ፡ ዘር ፡ ግን ፡ ቶሎ ፡ ልትወጡ
የዘራው ፡ ይመጣል ፡ በመከር ፡ ጊዜ
እንክርዳዱን ፡ ሊለይ ፡ ከጥሩ ፡ ፍሬ
ስንዴውን ፡ ሊያመርት ፡ ሃሌሉያ