ክስርትናዬ ፡ ጠቀመኝ (Kerestenayie Teqemegn)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ ፡ ተጓዳኝ
ቢያገኝም ፡ ቢያጣም ፡ አመሥጋኝ
ቢወድቅም ፡ እንኳን ፡ ይነሳል
ምርኮው ፡ ይመለሳል

አዝ፦ ክርስትናዬ ፡ ጠቀመኝ
ውሎ ፡ እያደረ ፡ ጣፈጠኝ

በሃዘን ፡ ጊዜ ፡ ደስታ
በለቅሶ ፡ ምድር ፡ ዕልልታ
በረሃብ ፡ ዘመን ፡ ጥጋቤ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ገንዘቤ

አዝ፦ ክርስትናዬ ፡ ጠቀመኝ
ውሎ ፡ እያደረ ፡ ጣፈጠኝ

የዓለም ፡ ኑሮ ፡ መራራ
ያልጠረበ ፡ ሸካራ
የለቅሶ ፡ አገር ፡ የዋይታ
በቃህ ፡ አለኝ ፡ ጌታ

አዝ፦ ክርስትናዬ ፡ ጠቀመኝ
ውሎ ፡ እያደረ ፡ ጣፈጠኝ

በጀሮ ፡ ስሚ ፡ ያወቅሁት
በግል ፡ ሕይወቴ ፡ አየሁት
ከቀን ፡ ወደ ፡ ቀን ፡ ደመቀ
ቤቴን ፡ እያሞቀ

አዝ፦ ክርስትናዬ ፡ ጠቀመኝ
ውሎ ፡ እያደረ ፡ ጣፈጠኝ