ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሁን (Kenie Gar Hun)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሁን ፡ በጨለመ ፡ ጊዜ
ጨልሟልና ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ እደር
ያለአንተ ፡ ረዳት ፡ በታጣ ፡ ጊዜ
የረዳተ ፡ ቢስ ፡ ረጅ ፡ አትለየኝ

የሕይወት ፡ ቀን ፡ ቶሎ ፡ ይቸኩላል
የምድር ፡ ተስፋም ፡ በቶሎ ፡ ያልፋል
በፍጥነትም ፡ ሁሉ ፡ ይለወጣል
የማትለወጥ ፡ ሆይ ፡ አትለየኝ

በየሰዓቱ ፡ ፊትህን ፡ እሻለሁ
ከሐዋሪያትህ ፡ ጋር ፡ እንደነበርህ
እኔን ፡ እንደ ፡ እነሱ ፡ አትለየኝ
በችግር ፡ በደስታ ፡ አትለየኝ

በየጊዜው ፡ እናፍቅሃለሁ
በጸጋህም ፡ ድልን ፡ አገኛለሁ
ያለ ፡ አንተ ፡ የሚመራኝ ፡ የለም
ማሸነፍ ፡ እንዳገኝ ፡ አትለየኝ