From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
Fet tekst
አዝ፦ ከሞትም ፡ ያድነዋል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ኢየሱስ ።
1. በሞት ፡ ጥላ ፡ የሚያድር ፡ በግዞት ፡ ሸለቆ
ጠላት ፡ የሚመታው ፡ አሸምቆ
ለአንበሳ ፡ መንጋጋ ፡ ለጣር ፡ የተጣለ
ነበረ ፡ ወገኔ ፡ የቆሰለ ።
አዝ፦ ከሞትም ፡ ያድነዋል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ኢየሱስ ።
2. ጌታ ፡ ደርሶለታል ፡ ወንጌል ፡ ልኮለታል
ሰማያዊ ፡ ብርሓን ፡ በርቶለታል
መልዕክተኞች ፡ ወጡ ፡ ጠላትን ፡ ገጠሙ
በመስቀሉ ፡ ጉልበት ፡ ድል ፡ አረጉት ።
አዝ፦ ከሞትም ፡ ያድነዋል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ኢየሱስ ።
3. ዓለምና ፡ ትርፏን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ገፍቶ
ከመታወቅ ፡ ይልቅ ፡ መናቅ ፡ መርጦ
ዘሩን ፡ ተሸክሞ ፡ በለቅሶ ፡ የሚዘራ
በደስታ ፡ ያጭዳል ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ ።
አዝ፦ ከሞትም ፡ ያድነዋል ፡ ከሞትም ፡ ያድናል
ከሞትም ፡ ያድናል ፡ ኢየሱስ ።
|