ከልቤ ፡ ላመስግነው ፡ ከልቤ (Kelebie Lamesgenew Kelebie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ከልቤ ፡ ላመስግነው ፡ ከልቤ (፫x)
አላየሁም ፡ አንዴ ፡ ቀን ፡ ሳትረዳኝ
አላየሁም ፡ ከፊቴ ፡ ስትርቀኝ
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እኮ (፬x)

ዓይኖቼ ፡ ማዳንህን ፡ አዩ ፡ ያ ፡ መከራዬ ፡ ተረሳ
እግዚአብሔር ፡ ሲደርስልኝ ፡ ሌሊቱ ፡ በአንድ ፡ አፍታ ፡ ነጋ
በፊቱ ፡ ሞገስ ፡ አገኘሁ ፡ ልመናዬ ፡ ተሰማልኝ
የራቡ ፡ ዘመን ፡ አበቃ ፡ ገበታን ፡ አዘጋጀልኝ

አዝ፦ ከልቤ ፡ ላመስግነው ፡ ከልቤ (፫x)
አላየሁም ፡ አንዴ ፡ ቀን ፡ ሳትረዳኝ
አላየሁም ፡ ከፊቴ ፡ ስትርቀኝ
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እኮ (፬x)

ታማኝነትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ ሳትቆጥብ ፡ ከፍ ፡ አደረከኝ
አስኬድከኝ ፡ በከፍታው ፡ ሊይ ፡ ጠላቴ ፡ በዓይኑ ፡ እንደያይ
ለእኔ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ጉልበቴ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
በሰጠኸኝ ፡ ዕድሜ ፡ ዘመን ፡ ላክብርህ ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ

አዝ፦ ከልቤ ፡ ላመስግነው ፡ ከልቤ (፫x)
አላየሁም ፡ አንዴ ፡ ቀን ፡ ሳትረዳኝ
አላየሁም ፡ ከፊቴ ፡ ስትርቀኝ
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እኮ (፬x)

እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው ፡ በለመለመ ፡ መስክ ፡ እሄዳለሁ
ውኃ ፡ ባለበት ፡ መንደር ፡ ውስጥ ፡ መኖሪያዬን ፡ አደርጋለሁ
ንጉሤ ፡ የሆንከውን ፡ አንተን ፡ በልቤ ፡ ሊይ ፡ ሾሜሃለሁ
ለዘለዓለም ፡ በቤትህ ፡ ውስጥ ፡ ተደላድዬ ፡ እኖራለሁ

አዝ፦ ከልቤ ፡ ላመስግነው ፡ ከልቤ (፫x)
አላየሁም ፡ አንዴ ፡ ቀን ፡ ሳትረዳኝ
አላየሁም ፡ ከፊቴ ፡ ስትርቀኝ
እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ እኮ (፬x)