ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እንሻገራለን (Kekeber Wede Keber Eneshageralen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እንሻገራለን
ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ ማነው ፡ ሚቋቋመን
ገና ፡ እናብባለን

ትላንት ፡ በእሳቱ ፡ ላይ ፡ ተራመድን
በእግዚአብሔር ፡ ፀጋ ፡ ሁሉን ፡ አለፍን
ማዕበል ፡ ወጀቡን ፡ የገሰጸው
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እንሻገራለን
ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ ማነው ፡ ሚቋቋመን
ገና ፡ እናብባለን

በትሩን ፡ በእጃችን ፡ አስይዞናል
በድንቅ ፡ በተአምራት ፡ ይመራናል
ሙሴን ፡ እንደረዳ ፡ ይረዳናል
በፈርዖንም ፡ ፊቴ ፡ ያቆመናል (፪x)

አዝ፦ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እንሻገራለን
ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ ማነው ፡ ሚቋቋመን
ገና ፡ እናብባለን

ደረቁ ፡ ስንባል ፡ ለምልመን
በእግዚአብሔር ፡ ታደሰ ፡ ኃይላችን
ገና ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ እንበዛለን
ወንጌሉን ፡ በስልጣን ፡ እንሰብካለን (፪x)

አዝ፦ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እንሻገራለን
ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ ማነው ፡ ሚቋቋመን
ገና ፡ እናብባለን

ጠላታችን ፡ ሰይጣን ፡ ወየውልህ
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ተዋጋህ
የራሱን ፡ ጦር ፡ ዕቃ ፡ አልብሶናል
ገና ፡ ብፁ ፡ ነገር ፡ ያወርሰናል (፪x)

አዝ፦ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እንሻገራለን
ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ ማነው ፡ ሚቋቋመን
ገና ፡ እናብባለን

ደርሶ ፡ ሚታደገው ፡ በመከራው
እግዚአብሔር ፡ በስሙ ፡ የጠራው
ምስጉን ፡ ነው ፡ ዘለዓለም ፡ ይኖራል
ለክብር ፡ ተጠርቷል ፡ ይከብራል (፪x)

አዝ፦ ከክብር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ እንሻገራለን
ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ ማነው ፡ ሚቋቋመን
ገና ፡ እናብባለን