ከከበደ ፡ ኃጢአቴ ፡ ወዴት ፡ ልሸሽ (Kekebede Hattiyate Wodet Lishesh Negne)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከከበደ ፡ ኃጢአቴ ፡ ወዴት ፡ ልሸሽ
ኦ! አምላኬ
በጣም ፡ እጨነቃለሁ
ሕግህን ፡ ሁሉ ፡ አፍርሼ
ሩቅም ፡ ከአንተ ፡ ሸሽቼ
ፍርድህን ፡ እፈራለሁ
ነፍሴንም ፡ ሐዘን ፡ ደቆሰው
ልቤንም ፡ ጸጸት ፡ ሰበረው
ኦ! ጌታዬ ፡ ራራልኝ
መድኃኒትም ፡ ሁንልኝ

ኦ! ኢየሱስ ፡ ቃልህ ፡ ሕይወት ፡ ነው
ለነፍሴ ፡ ጤናም ፡ ጣፋጭ ፡ ነው
ልቀበለውም ፡ እሻለሁ
ወዳለም ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቷል
ዕዳዬን ፡ ከፈለ ፡ ይላል
በእርሱም ፡ እድናለሁ
ቀማኛውን ፡ የተቀበለው
በገነትም ፡ ያሳረፈው
እኔንም ፡ እንዲቀበል
ይለኛል ፡ ቅዱስ ፡ ወንጌል

ኦ! ኢየሱስ ፣ ኦ! የዳዊት ፡ ልጅ
ወደ ፡ አንተ ፡ ዓይንና ፡ እጅ
እኔ ፡ እዘረጋለሁ
የረከስሁ ፡ እኔን ፡ አጥራኝ
ከኃጢአትም ፡ ዕድፍ ፡ አንጻኝ
በአንተ ፡ አምናለሁ
የጠፋች ፡ በግም ፡ ነበርሁኝ
በአንተ ፡ ግን ፡ ተገኘሁኝ
አኑረኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
አንተ ፡ የ ም ት ራ ራ