ከዕለታት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ አሁን (Keiletat Aand Qen Ahun)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ከዕለታት ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ አሁን
ከእኛ ፡ አልፏል
ፀሐይ ፡ ሲጨልም ፡ ሌሊቱን
አምላክ ፡ ልኮልናል

ግን ፡ እርሱ ፡ አይለዋወጥም
አያልቅም ፡ ፍቅሩ
ቀማችም ፡ ሌታችንም
ነው ፡ እንደምክሩ

ኦ! አምላክ ፡ በእጅህ ፡ ልሁን
ጉዳትንም ፡ አልፍራ
ሲነጋም ፡ ቅዱስ ፡ ስምህን
በውዳሴ ፡ ልጥራ

ግን ፡ በዚህ ፡ ሌት ፡ የሞት ፡ መልዓክ
የጠራኝ ፡ እንደሆን
የአንተ ፡ ነኝ ፡ ኦ! ቸር ፡ አምላክ
ከአንተም ፡ ዘንድ ፡ ልሆን