From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ እንወድቃለን ፡ በፊትህ
ልናመልክህ ፡ አንተን ፡ ልናከብርህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አምላካችን ፡ ነህና
ይኸው ፡ መጣን ፡ ልንሰዋ ፡ ምሥጋና (፫x)
ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ የዋጀኸን
ከአራቱም ፡ ማዕዘን ፡ ያመጣኸን
በስምህ ፡ የተጠራን ፡ ልጆችህ
ዙፋንህ ፡ ስር ፡ አለን ፡ ልናመልክህ
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ልናደርግህ
አዝ፦ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ እንወድቃለን ፡ በፊትህ
ልናመልክህ ፡ አንተን ፡ ልናከብርህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አምላካችን ፡ ነህና
ይኸው ፡ መጣን ፡ ልንሰዋ ፡ ምሥጋና (፫x)
ከጨለማው ፡ ዓለም ፡ ያወጣኸን
ወደ ፡ ታላቅ ፡ ብርሃን ፡ ያመጣኸን
ከምርኮ ፡ ሃገርም ፡ ያፈለሰህን
በፉጨትም ፡ ጠርተህ ፡ ያቀረብከን
ልጆች ፡ እንሰግድልሃለን
አዝ፦ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ እንወድቃለን ፡ በፊትህ
ልናመልክህ ፡ አንተን ፡ ልናከብርህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አምላካችን ፡ ነህና
ይኸው ፡ መጣን ፡ ልንሰዋ ፡ ምሥጋና (፫x)
የሠማይ ፡ መላዕክቶች ፡ በሙሉ
በምድርም ፡ ያላችሁ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ላለው ፡ አምላካችን
በአንድነት ፡ እንስገድ ፡ ተንበርክከን
አናምልከው ፡ ክብርን ፡ እየሰጠን
አዝ፦ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ እንወድቃለን ፡ በፊትህ
ልናመልክህ ፡ አንተን ፡ ልናከብርህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አምላካችን ፡ ነህና
ይኸው ፡ መጣን ፡ ልንሰዋ ፡ ምሥጋና (፫x)
እስትንፋስን ፡ ሰርተህ ፡ የፈጠርከን
በልጅህ ፡ ሞት ፡ ዳግም ፡ የወለድከን
ሁለት ፡ ጊዜ ፡ ሰርተህ ፡ ያበጀኸን
በዙፋንህም ፡ ቀኝ ፡ ያስቀመጥኸን
ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ክበርልን
አዝ፦ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ እንወድቃለን ፡ በፊትህ
ልናመልክህ ፡ አንተን ፡ ልናከብርህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አምላካችን ፡ ነህና
ይኸው ፡ መጣን ፡ ልንሰዋ ፡ ምሥጋና (፫x)
ጨረቃና ፡ ፀሐይ ፡ ከዋክብቶች
ምድርና ፡ ሠማይ ፡ ሠማያቶች
ፍዑዛን ፡ ፍጥረታትም ፡ ሁላችሁ
እንስሳትም ፡ እስትንፋስ ፡ ያላችሁ
ስገዱለት ፡ በሙሉ ፡ ልባችሁ
አዝ፦ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ እንወድቃለን ፡ በፊትህ
ልናመልክህ ፡ አንተን ፡ ልናከብርህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ አምላካችን ፡ ነህና
ይኸው ፡ መጣን ፡ ልንሰዋ ፡ ምሥጋና (፫x)
|