ከፍ ፡ በል (Kef Bel)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝከፍ (፬x) ፡ በል
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በል
ከፍ (፬x) ፡ በል
ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ በል (፪x)

ብንወጣና ፡ ብንወርድም ፡ አናገኝም ፡ ለእኛ
እንዳንት ፡ ያለ ፡ አመል ፡ ያለው ፡ የሕይወት ፡ ጓደኛ
ስለዚህም ፡ እንቀርባለን ፡ በፊትህ ፡ እንደገና
አሁንም ፡ አሁንም ፡ ይድረስህ ፡ ምሥጋና

አዝከፍ (፬x) ፡ በል
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በል
ከፍ (፬x) ፡ በል
ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ በል (፪x)

በገናችንም ፡ ይነሣ ፡ ቅኔውም ፡ ይደርደር
ከበሮው ፡ ይመታ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ክብር
በእንቢልታ ፡ በዕልልታ ፡ ክበር ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ
ሕዝብህን ፡ የምትታደግ ፡ የእኛ ፡ አለኝታ

አዝከፍ (፬x) ፡ በል
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በል
ከፍ (፬x) ፡ በል
ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ በል (፪x)

ሐሩሩንም ፡ ተወጣነው ፡ ምድረ ፡ በዳውን ፡ አለፍን
ጠላታችንን ፡ ድል ፡ ነሣን ፡ በአንተ ፡ ተደገፍን
አንደበታችን ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና ፡ ያወጣል
ተመስገን ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ጌታችን ፡ ይልሃል

አዝከፍ (፬x) ፡ በል
ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በል
ከፍ (፬x) ፡ በል
ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ በል (፪x)