ክቡር ፡ ኃይል ፡ አለው (Kebur Hayl Alew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

የተናቀ ፡ ሰው ፡ የተላው ፡ ነበር
ያ ፡ የሞተልኝ ፡ የሞተልኝ
ተጨነቀ ፡ ተሰቃየም ፡ በጣር
ክቡር ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ በደሙ

አዝ፦ ክቡር ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ በደሙ
በክቡር ፡ በጉ ፡ ደም
ኃይል ፡ አለው ፡ ግሩም ፡ ስራ ፡ የሚሰራ
በከበረው ፡ በበጉ ፡ ደም

የጌታዬን ፡ ደም ፡ አስባለሁ ፡ ወይ?
ያ ፡ የሞተልኝን ፡ የኢየሱሴን
ትረሻለሽ ፡ ነፍሴ ፡ የቀራንዮን
ግሩም ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ በደሙ

አዝ፦ ክቡር ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ በደሙ
በክቡር ፡ በጉ ፡ ደም
ኃይል ፡ አለው ፡ ግሩም ፡ ስራ ፡ የሚሰራ
በከበረው ፡ በበጉ ፡ ደም

ኢየሱስ ፡ ጌታህን ፡ ታስባለህ ፡ ወይ?
ያን ፡ የሞተውውን ፡ የሞትውን
እንባው ፡ የራሰው ፡ ጌቴሰማኔን
ክቡር ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ በደሙ

አዝ፦ ክቡር ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ በደሙ
በክቡር ፡ በጉ ፡ ደም
ኃይል ፡ አለው ፡ ግሩም ፡ ስራ ፡ የሚሰራ
በከበረው ፡ በበጉ ፡ ደም

የጌታህን ፡ ህማም ፡ ትረሳ ፡ ይሆን?
ያን ፡ የሞተውን ፡ የሞተውን
ንጹህ ፡ ደሙ ፡ ያነጸውን ፡ ሁሉን
ብርቱ ፡ ህይል ፡ አለው ፡ በደሙ

አዝ፦ ክቡር ፡ ኃይል ፡ አለው ፡ በደሙ
በክቡር ፡ በጉ ፡ ደም
ኃይል ፡ አለው ፡ ግሩም ፡ ስራ ፡ የሚሰራ
በከበረው ፡ በበጉ ፡ ደም