ክብሬ ፡ ትዘምርልህ (Kebrie Tezemereleh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እጆቼ ፡ ያጨብጭቡ ፡ ምሥጋናን ፡ ይሰዉልህ
እግሮቼም ፡ ይዘዙልህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ
አንደበቴም ፡ ያውራ ፡ ይታወጅ ፡ ማዳንህ
ትናቀኝ ፡ ዛሬ ፡ ሜልኮል ፡ ክብሬ ፡ ትዘምልህ

አዝክብሬ ፡ ትዘምርልህ (፪x)
ክብር ፡ ይሁልህ

ለእኔ ፡ ውርደት ፡ ይምሰል ፡ ግን ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ይሁን
እዘምራለሁ ፡ ዛሬም ፡ በሜልኮል ፡ ዐይን ፡ ፊት ፡ ልቅለልልህ
ድምጺን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርጌ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ላዚምልህ
ያስተጋቡ ፡ ሠማያት ፡ ክብሬ ፡ ትዘምርልህ

አዝክብሬ ፡ ትዘምርልህ (፪x)
ክብር ፡ ይሁልህ

ዘወትር ፡ በሙሉ ፡ ኃይሌ ፡ በመፈሴ ፡ ላምልክህ
ይናቀኝ ፡ ያየኝ ፡ ሁሉ ፡ ክብሬ ፡ ትዘምርልህ
በምሥጋና ፡ ሆ! ፡ እያልኩኝ ፡ ልዘምር ፡ ወደ ፡ ደጆችህ
የምሥጋና ፡ መሥዋዕትን ፡ ለክብርህ ፡ ልጠንልህ

አዝክብሬ ፡ ትዘምርልህ (፪x)
ክብር ፡ ይሁልህ

ፍጡር ፡ ሁሉ ፡ በቋንቋ ፡ አንተን ፡ ያመስግን
መላእክቶችም ፡ በላይ ፡ ሌት ፡ ከቀን ፡ ይስገዱልህ
ታርደሃልና ፡ ስለእኔ ፡ አዳኜ ፡ ላመስግንህ
ይበለኝ ፡ ያለውን ፡ ሰው ፡ ክብሬ ፡ ትዘምርልህ

አዝክብሬ ፡ ትዘምርልህ (፪x)
ክብር ፡ ይሁልህ