ከበረዶ ፡ እነፃለሁ (Keberedo Enetsalehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ፍፁም ፡ መሆንን ፡ እወዳለሁ
ኢየሱስ ፡ ለዘለዓለም
በውስጤ ፡ እንድትኖር
ጣዖትን ፡ ስበር ፡ ጠላትን ፡ አርቀው

አዝ፦ እጠበኝ ፡ ከበረዶ ፡ እነፃለሁ ፡ እነፃለሁ
ከበረዶ ፡ ይልቅ ፡ እጠበኝ
ከበረዶ ፡ እነፃለሁ

ኦ ፡ ጌታ ፡ ከዙፋንህ ፡ ተመልከተኝ
ፍፁም ፡ መሥዋዕትን ፡ ለማቅረብ ፡ እርዳኝ
ያለኝን ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ

አዝ፦ እጠበኝ ፡ ከበረዶ ፡ እነፃለሁ ፡ እነፃለሁ
ከበረዶ ፡ ይልቅ ፡ እጠበኝ
ከበረዶ ፡ እነፃለሁ

በትሕትና ፡ ልኑር ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ከእግርህ ፡ በታች ፡ ሆኜ ፡ ላመስግንህ
የፈሰሰውን ፡ ደምህን ፡ እንዳስታውስ

አዝ፦ እጠበኝ ፡ ከበረዶ ፡ እነፃለሁ ፡ እነፃለሁ
ከበረዶ ፡ ይልቅ ፡ እጠበኝ
ከበረዶ ፡ እነፃለሁ

በትዕግሥት ፡ ስጠብቅህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
አሁን ፡ ና ፡ አዲሱን ፡ ልብ ፡ ፍጠርልኝ
ለፈለገህ ፡ ሁሉ ፡ እምቢ ፡ አትልም

አዝ፦ እጠበኝ ፡ ከበረዶ ፡ እነፃለሁ ፡ እነፃለሁ
ከበረዶ ፡ ይልቅ ፡ እጠበኝ
ከበረዶ ፡ እነፃለሁ