ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ (Keber Yehunelet Lenegusu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ ፡ አሜን
ለንጉሡ ፡ ተነሡ
በገና ፡ መሰንቆ ፡ ከበሮ ፡ ያዙና
እንሰዋ ፡ አሜን ፡ እንሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)

ሕዝቡን ፡ ለተኩላዎች ፡ አሳልፎ ፡ አልሰጠም ፡ ሸሽጐናል
በክንፉ ፡ ከልሎ ፡ እዚህ ፡ አድርሶናል ፡ ታድጐናል
ለሚነጣጠቁ ፡ ለጥርስ ፡ ንክሻ ፡ አልተወንም
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እንደ ፡ ጠላት ፡ ዛቻ ፡ አልጠፋንም

አዝ፦ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ ፡ አሜን
ለንጉሡ ፡ ተነሡ
በገና ፡ መሰንቆ ፡ ከበሮ ፡ ያዙና
እንሰዋ ፡ አሜን ፡ እንሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)

በታላቅ ፡ ማዳኑ ፡ ሕዝቡን ፡ የሚታደግ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ
ለሥሙ ፡ የሚቀና ፡ ለሕዝቡ ፡ ተበቃይ ፡ የሚረታ
ተነሡ ፡ እናመስግን ፡ ፈቅደን ፡ እንወድሰው ፡ ጠላት ፡ ይፈር
ዕልልታው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ተፈተን ፡ እንቁም ፡ ሥሙ ፡ ይክበር

አዝ፦ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ ፡ አሜን
ለንጉሡ ፡ ተነሡ
በገና ፡ መሰንቆ ፡ ከበሮ ፡ ያዙና
እንሰዋ ፡ አሜን ፡ እንሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)

ተነሡ ፡ እንጓደድ ፡ በኃያሉ ፡ ሥሙ ፡ እንነሣ
ሌላማ ፡ ማን ፡ አለን ፡ ከቶ ፡ የማይናወጥ ፡ የሚያስመካ?
ሰይጣንም ፡ ይመልከት ፡ ጌታችን ፡ ሲከብር ፡ ኃይሉ ፡ ይቅለጥ
በምሥጋና ፡ እንውጣ ፡ የጨለማው ፡ ሥራ ፡ እንዲገለጥ

አዝ፦ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ ፡ አሜን
ለንጉሡ ፡ ተነሡ
በገና ፡ መሰንቆ ፡ ከበሮ ፡ ያዙና
እንሰዋ ፡ አሜን ፡ እንሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)

በማይናወጠው ፡ ሰላሙን ፡ የሞላን ፡ ኢየሱስ ፡ ይክበር
ዕለት ፡ ዕለት ፡ ለእኛ ፡ ሆኖናል ፡ መከታ ፡ የእሣት ፡ ቅጥር
ስለዚህ ፡ አድራጐቱ ፡ ምንከፍለው? ፡ የለንም ፡ ከምሥጋና ፡
ተነሡ ፡ እናወድሰው ፡ በእንቢልታ ፡ መለከት ፡ በበገና

አዝ፦ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ ፡ አሜን
ለንጉሡ ፡ ተነሡ
በገና ፡ መሰንቆ ፡ ከበሮ ፡ ያዙና
እንሰዋ ፡ አሜን ፡ እንሰዋ ፡ ምሥጋና (፪x)