ክብር ፡ ይሁን (Keber Yehun)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝክብር ፡ ይሁን (፫x)
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ
ልበለው ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ

ጌታ ፡ ስላከበረኝ ፡ እኔ ፡ ዛሬ ፡ ክብር ፡ ነኝ
በዝቶልኛል ፡ ሰላሙ
ክብር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ

አዝክብር ፡ ይሁን (፫x)
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ
ልበለው ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ

ክብር ፡ ይሁን ፡ ለስሙ
አንጽቶኛል ፡ በደሙ
ሕይወት ፡ ሰጥቶኛል ፡ ሞቱ
አስታረቀኝ ፡ ከአባቱ

አዝክብር ፡ ይሁን (፫x)
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ
ልበለው ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ

ልጁ ፡ ሆኛለሁ ፡ ዛሬ
ባሪያ ፡ መሆኔም ፡ ቀረ
ኀጢአትም ፡ አይገዛኝም
ጋርዶኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም

አዝክብር ፡ ይሁን (፫x)
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ
ልበለው ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ

ከሞት ፡ ወጥመድ ፡ አምልጬ
ዘንዶውን ፡ በእግሬ ፡ ረግጬ
ሕያው ፡ ሆኜ ፡ ኖራለሁ
ለክብሩ ፡ ዘምራለሁ

አዝክብር ፡ ይሁን (፫x)
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ
ልበለው ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ

አየሁኝ ፡ የእርሱን ፡ ግርማ
ወጣሁኝ ፡ ከጨለማ
በርቶልኛል ፡ ብርሃኑ
ለእኔስ ፡ ወጣልኝ ፡ ቀኑ

አዝክብር ፡ ይሁን (፫x)
ለበጉ ፡ ለኢየሱስ
ልበለው ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ