ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (Keber Yegebahal Yegna Amlak)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ፡ ምሥጋናም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)
ክብር ፡ ሃሌሉያ (፬x)

እግዚአብሔር ፡ ነገሠ ፡ ክብር ፡ ለበሰ
ታጠቀ ፡ ኃይልንም ፡ ለበሰ
ዓለምን ፡ አፀናት ፡ አቆማት
ምሕረትህ ፡ ድንቅ ፡ ዘለዓለማዊት

አዝ፦ ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ፡ ምሥጋናም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)
ክብር ፡ ሃሌሉያ (፬x)

ዘለዓለማዊ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ
ዝግጁ ፡ ነው ፡ ከጥንት ፡ ዙፋንህ
ወንዞች ፡ ከፍ ፡ አረጉ ፡ ድምጻቸውን
ተራሮችም ፡ ጤሱ ፡ ሰጡ ፡ ክብርህን

አዝ፦ ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ፡ ምሥጋናም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)
ክብር ፡ ሃሌሉያ (፬x)

ከብዙ ፡ ውሆችም ፡ ድምፅ ፡ ይልቅ
ከታላቅ ፡ ሞገድም ፡ ድምፅ ፡ ይልቅ
ጌታችን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኃያል ፡ ድንቅ
ምሥክርህ ፡ ታማኝ ፡ አንተ ፡ ታላቅ

አዝ፦ ክብር ፡ ይገባሃል ፡ የእኛ ፡ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ፡ ምሥጋናም ፡ ለአንተ ፡ ነው (፪x)
ክብር ፡ ሃሌሉያ (፬x)