ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን (Keber Lersu Yehun)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
ክብር ፡ ሃሌሉያ
ደስታ ፡ ብቻ ፡ ይሆናል
ሥቃይ ፡ የለም ፡ በዚያ

ታላቁ ፡ ቀን ፡ ቀርቧል ፡ በጣም ፡ ደስ ፡ ይበለን
ጌታችን ፡ ሲገለጥ ፡ ከምድር ፡ ሊወስደን
ከቤቱ ፡ ሊያገባን

አዝ፦ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
ክብር ፡ ሃሌሉያ
ደስታ ፡ ብቻ ፡ ይሆናል
ሥቃይ ፡ የለም ፡ በዚያ

ምድር ፡ ልትዘጋጅ ፡ በእሣት ፡ ልትጠራ
ፅልመት ፡ ሲያለብሳት ፡ የአቶሚክ ፡ አቧራ
ብርሃን ፡ ለእኛ ፡ በራ

አዝ፦ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
ክብር ፡ ሃሌሉያ
ደስታ ፡ ብቻ ፡ ይሆናል
ሥቃይ ፡ የለም ፡ በዚያ

የበጉ ፡ ሠርግ ፡ ቀርቧል ፡ ልዘጋጅ ፡ ወንድሜ
ጥሪ ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተጽፎ ፡ በስሜ
ይመስገን ፡ ጌታዬ

አዝ፦ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
ክብር ፡ ሃሌሉያ
ደስታ ፡ ብቻ ፡ ይሆናል
ሥቃይ ፡ የለም ፡ በዚያ

ነቅቶ ፡ የሚጠብቅ ፡ ልብሱ ፡ እንዳይጠፋበት
ያገኛል ፡ ከአምላኩ ፡ ትርፍ ፡ ያለውን ፡ ሕይወት
በላይ ፡ በአምላኬ ፡ ቤት

አዝ፦ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን
ክብር ፡ ሃሌሉያ
ደስታ ፡ ብቻ ፡ ይሆናል
ሥቃይ ፡ የለም ፡ በዚያ