ክብር ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ለአንተ (Keber Lante Keber Lante)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ለአንተ
ኢየሱስ ፡ ሆይ! ክብር ፡ ለአንተ
ክብር ፡ ለአንተ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ለአንተ

ሕይወቴን ፡ በደምህ ፡ ለዋጀሃት
ከኃጢአት ፡ ማዕበል ፡ ላወጣሃት
ክብር ፡ ለአንተ ፡ ይሁን ፡ ኢየሱሴ ፡ ሆይ!
የሞትክልኝ ፡ ለእኔ ፡ ወርደህ ፡ ከላይ

አዝ፦ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ለአንተ
ኢየሱስ ፡ ሆይ! ክብር ፡ ለአንተ
ክብር ፡ ለአንተ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ለአንተ

የመላዕክት ፡ ምግብ ፡ እያዘነብህ
ከዓለት ፡ ድንጋይ ፡ ውሃን ፡ እያፈለቅህ
ሕዝብህን ፡ በቀን ፡ በሌት ፡ በእጅህ ፡ የመራህ
ክብር ፡ ክብር ፡ ለአንተ ፡ አማኑኤል

አዝ፦ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ለአንተ
ኢየሱስ ፡ ሆይ! ክብር ፡ ለአንተ
ክብር ፡ ለአንተ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ለአንተ

የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ላወድስህ
አለኝታ ፡ ተስፋዬ ፡ አንባዬ ፡ ነህ
አልፋና ፡ ዖሜጋ ፡ አማኑኤል
ሳወድስህ ልኑር ፡ ለዘለዓለም

አዝ፦ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ለአንተ
ኢየሱስ ፡ ሆይ! ክብር ፡ ለአንተ
ክብር ፡ ለአንተ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ለአንተ

የሕይወቴ ፡ አለኝታ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
እንዳመሰግንህ ፡ ልቤን ፡ ቀድስ
የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ ጌታ ፡ ባርከው
እንዳልሆን ፡ ዕንቅፋት ፡ ለጠራኸው

አዝ፦ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ለአንተ
ኢየሱስ ፡ ሆይ! ክብር ፡ ለአንተ
ክብር ፡ ለአንተ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ክብር ፡ ለአንተ